አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የተመድ ዋና ጸሀፊ ልዩ ተወካይና ዩኤንሶም ሀላፊ ጋር ተወያዩ::
የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ ልዩ ተወካይና በተባበሩት መንግስታት የሶማሊያ ድጋፍ ተልዕኮ(ዩኤንሶም) ሀላፊ ካትሪዮና ላንግ ጋር ተወያዩ፡፡ በውይይታቸውም አምባሳደር ታዬ፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ቀጣይነት ያለው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡ ካትሪዮና ላንግ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ያደረገችውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡ በተጨማሪም በውይይቱ ወቅት ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ…
