ክልሉ ያለዉን እምቅ አቅም ተጠቅሞ በዜጎች ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት:-የሱፐርቪዥን ቡድን::
የኢፌዲሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን ላለፉት 10 ቀናት በክልሉ ያካሄደውን ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ግብረ- መልስ ማጠቃለያ ውይይት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ በክልሉ በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ የተሰሩ የተገኙ ውጤቶች ለማስቀጠል ክህሎት መር ተቋማዊ ግንባታ በማጠናከር በየአካባቢ ተገንብተው ወደስራ ያልገቡ የማምራቸ እና መሸጫ ሼዶችን አጠናቆ ወደ ስራ ማስገባት…
