Trendings

BLOGS

28ኛው የአድዋ ድል መታሠቢያ በአልን ለማክበር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ፍፁም ሠላማዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አስታወቀ።

የፀጥታና ደህነት የጋራ ግብረ ሃይሉ የፊታችን የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከበረው 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በአል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ለማስቻል በወጣው የማስፈፀሚያ እቅድ ላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ሰላም አዳራሽ ላይ ውይይት አድርጓል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻ ሀላፊ ጀነራል ተስፋዬ አያሌው በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት የመላው ኢትዮጵያውያን በዓል የሆነው የአድዋ ድል በአል ሲከበር ምንም…

Read More

በክልሉ የቡና ምርት የግብይትና ጥራት ቁጥጥር ስርዓትን ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት አለባቸው፦ አቶ ማስረሻ በላቸው::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቡናና ሻይ፣ ቅመማ ቅመም ባለስልጣን የ2016 ምርት ዘመን የቡና ምርትና ግብይት ጥራት ቁጥጥር አስተባባሪ ግበረ-ኃይል የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሄደ። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ቡናን በአግባቡ በማምረት ለአለም ገበያ ማቅረብ የሀገሪቱን ጥቅም ማስከበር በመሆኑ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ዘርፉን ትኩረት ሰጥተው መምራት እንደሚገባቸው…

Read More

ኢትዮጵያና ኔዘርላንድ በሞጆ ደረቅ ወደብ ቀዝቃዛ መጋዘን ለመገንባት የሚውል 10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፋ ስምምነት ተፈራረሙ

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ሄንክ ያን ተፈራርመዋል፡፡ ድጋፍ በሞጆ እየተገነባ ላለው ቀዝቃዛ መጋዘን አዲስ ፖርት ፕሮጀክት ምዕራፍ አንድ የሚውል ነው። በስምምነቱ መሰረት የሚገነባው መጋዘን ኢትዮጵያ ወደ ውጭ የምትልካቸው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ሳይበላሹ ለማቅረብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡

Read More

”አድዋ የመደመር ተምሳሌታዊ አርማ” በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

በፓናል ውይይቱ ላይ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ፣ የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ መኮንኖች፣ የምክር ቤት አባላት፣ አርበኞችና ምሁራን ተገኝተዋል። በኢዜአ አዲሱ ስቲዲዮ እየተካሄደ ባለው የፓናል ውይይት የአድዋ ድል የአብሮነትና የአንድነት ተምሳሌት፣ የጥቁር ህዝቦች ነፃነት የነበረው ሚና እንዲሁም የዚህ ዘመን አድዋ ምን መሆን አለበት…

Read More

የፌደራል ስርዓቱን ለማጠናከር እና የፍትህ ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::

የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የፌዴራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፌደራል ስርዓቱን ለማጠናከር እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱን ለማሳለጥ የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት እና የፌዴራል ፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት በሕግ የተሠጣቸውን ተግባራትንና ኃላፊነቶችን መነሻ በማድረግ የጋራ ግቦቻቸውን ለማሳካት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተወያይተው ተፈራርመዋል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር በወቅቱ እንዳሉት…

Read More

128ኛው የዓድዋ ድል በዓል የሰራዊታችንን ድሎችና አኩሪ ገጽታ በሚያጎላ መልኩ ይከበራል፡ – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት::

128ኛው የዓድዋ ድል በዓል የሰራዊታችንን ድሎችና አኩሪ ገጽታ በሚያጎላ መልኩ ይከበራል ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም 128ኛው የዓድዋ ድል በዓል አከባበርን በተመለከተ እንደተናገሩት ፥ አምና 127ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አከባበርን የሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲያስተባብር ተደርጎ ከፍተኛ በሆነ ሀገራዊ ንቅናቄ በድምቀት…

Read More

ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥር የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው፡ – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥራ የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ዘገባ ለመስራት ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ለ37ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን አስታውሰዋል፡፡…

Read More

በአዕምሮ እና በስጋ መቀንጨርን ለመከላከል የምግብስርዓትና የስርዓተ ምግብ ፕሮግራሞችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተገለጸ::

በምግብስርዓትና ስርዓተ ምግብ ፕሮግራም ዙሪያ ያተኮረ ክልል አቀፍ ውይይት ተደርጓል። በውይይቱ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት በአዕምሮ እና በስጋ መቀንጨርን ለመከላከል የምግብ ስርዓትና የስርዓተ ምግብ ፕሮግራሞችን በቅንጅት መምራት እንደሚገባ ተናግረዋል። የምግብ ስርዓትና ስርዓተ ምግብ ፕሮግራም የተጠናከረ መሆን ጤናማ እና አምራች ትውልድ እንዲኖር ያግዛል ሲሉም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም የተጀመሩ የምግቤን ከጓሮዬና የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በማጠናከር…

Read More

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ 23 ነጥብ 46 ቢሊዮን ብር ገቢ አገኘ::

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ 23 ነጥብ 46 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ በ2016 በጀት አመት አጋማሽ በሺፒንግ ዘርፍ ፣ በጭነት አስተላላፊነት ፣ በወደብና ተርሚናል አገልግሎት እንዲሁም በኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ የተለያዩ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጿል። በዚህም በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከሚሰጡ አገልግሎቶችና ከሌሎች የገቢ ምንጮች 17 ነጥብ 23 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ…

Read More