በክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመከላከያ እና ለመቆጣጠር የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መስራት እንሚጠበቅ ተጠቆመ::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት የሲ.ዲ.ሲ ፕሮጀክት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በክልሉ ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ባለፉት 6 ወራት ኤች አይ ቪ ኤድስ ከመከላከያ እና ከመቆጣጠር አንፃር በርካታ ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረው በዚህ…
