የሙስና ትግሉን በዘላቂነት ለማስቀጠል በአሰራር ብቻ የሚመራ ጠንካራ ተቋም መገንባት ይገባል፦ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ
”ትውልድን በስነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል 22ኛ ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ክልላዊ ማጠቃለያ መርሐግብር በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ንጉሴ ወ/ጊዮርጊስ ሙስና ለሀገር ዕድገት ማነቆ በመሆኑ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መታገል እንደሚገባ ተናግረዋል። በክልሉ ህብረተሰቡ ባሳተፈ ትግል ሙስናን የመከላከል አቅም ማሳደግ መቻሉን ጠቁመው በሙስናና ብልሹ…
