በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ ስልጠና ላይ በተገኘው ክህሎት አመራሩ በአግባቡ በመጠቀም እቅዶች ማሳካት እንደሚገባ ተገለፀ።
በክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ በአቶ ነጋ አበራ የተመራው የድጋፍ እና ክትትል ቡድን ከምዕራብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ጋር በቀጣይ ሥራዎች እቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል። በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደተናገሩት አመራሩ በመፈጠር፤ በመፍጠን እና በዝላይ ዉጤት በሚመጣ መንገድ እና አማራጮች…
