ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እያደረገው ያለውን ቅድመ ዝግጅት አጠናክሮ እንዲቀጥል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ። ቋሚ ኮሚቴው የቦርዱን የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት አፈጻጸምን ገምግሟል። በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ…
