Trendings

ባለፋት ዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ያለፉት ዘጠኝ ወራት የቡና ንግድ አፈፃፀምን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ባለፋት ዘጠኝ ወራት ወደ ውጭ ከተላከ የቡና ምርት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል። ባለፉት ዘጠኝ ወራት 299 ሺህ 607 ቶን ቡና በመላክ ከእቅድ በላይ ማሳካት መቻሉንም ጠቅሰው፤…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሀኖይ ቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2025 የፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ ላይም ይሳተፋሉ። በቆይታቸው ከቬይትናም የፀሃይ ኃይል ማመንጫዎች በማምረት ወደ ውጭ የሚልከውን ቶዮ ሶላር የተባለውን ፋብሪካ ጎብኝተዋል። ድርጅቱ በቅርቡ በሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በመግባት በኢትዮጵያ ሥራ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅቱ ከፀሃይ ኃይል…

Read More

ቤላሩስ ከኢትዮጵያ ጋር በቴክኖሎጂ ዘርፍ በትብብር መስራት እንደምትፈልግ ገለጸች

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ከቤላሩስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዤንኮፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት በቴክኖሎጂ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፥ ቤላሩስ በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ ለኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ በማመስገን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና በሌሎች ዘርፎች አበረታች ውጤት እያስመዘገበች መሆኑን ጠቁመው፥ ከአጋር ሀገራት…

Read More

ኢትዮጵያ እና ቤላሩስ የጋራ ተጠቃሚነታቸውን በሚያረጋግጡ መስኮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ገለጹ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዜንኮቭን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ሚኒስትሮቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ እ.አ.አ በኦክቶበር ወር 2024 በሩሲያ ካዛን ከተካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት አንስተዋል። ውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ጌዲዮን (ዶ/ር) ኢትዮጵያ…

Read More

njjjሀገራዊ ልማት የሁሉንም ርብርብ ስለሚጠይቅ ምልዓተ ሕዝቡን አስገንዝቦ ማነሣሣት ላይ ሊተኮር ይገባል፦ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ

ሀገራዊ ልማት እና ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ የሚቻለዉ ቀጣይነት ያለው የምልዓተ ሕዝቡ ተሳትፎ በመሆኑ ሀገራዊ ትልሞችን እና የመዳረሻ ግቦችን ማስገንዘብ ላይ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ እንዲያተኩር የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ “ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለኢትዮጵያ መንሰራራት” በሚል መሪ መልእክት ለክልል እና ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በአዲስአበባ እየተሰጠ ባለው ሥልጠና…

Read More

ባለፉት 9 ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች ሳያዘናጉን ለበለጠ ከፍታ ሊያነሳሱን ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ ተጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በግምገማው የሚቀጥሉትን 3 ወራት ሥራዎቻችንን እቅድ ለማጠናከር የሚረዱ ውይይቶችን እናካሂዳለን ብለዋል። እስካሁን ያሳካነው የሥራ ውጤት ሰፊ ቢሆንም ስኬታችን ሳያዘናጋን ለበለጠ ከፍታ የሚያነሳሳን ሊሆን ይገባል ነው ያሉት ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Read More

አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍ ማድረግ ይገባል – ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)

አምራች ኢንዱስትሪዎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለፁ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ነው፡፡ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በማቃለል የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ሊደገፉ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ማነቆ…

Read More

የኮሙኒኬሽን ሥራን ዓላማ ተኮር ማድረግ እንደሚገባ ተመላከተ

ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ የኮሙኒኬሽን ሥራችንን ዓላማ ተኮር ማድረግ አለብን ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶር) አስገነዘቡ፡፡ “ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለኢትዮጵያ መንሠራራት” በሚል መሪ ሐሳብ ለክልል እና ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው የዐቅም ግንባታ ስልጠና እንደቀጠለ ነው፡፡ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የበይነ-መረብ ዐውዱ የመረጃ ፍሠቱን ከአንድ ወደ ባለብዙ…

Read More

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት የተፈራረሙትን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር ይገባል- ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ሕብረት የተፈራረሙትን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በአውሮፓ ሕብረት የውጭ ግንኙነት አገልግሎት የኢኮኖሚ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሳይመን ሞርዱ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እና አውሮፓ ሕብረት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በየጊዜው…

Read More