Trendings

የክልሉ ጤና ቢሮ በክልሉ የጤና አገልግሎቶችን ለማሳለጥ የሚያስችሉ አምቡላሶችን ለዞኖች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ያስረከቡት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንዳሉት አምቡላሶቹ የእናቶችና ህጻናት ጤናን ለማጎልበት እንዲሁም ለድንገተኛ ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውን ገልፀዋል ። በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት ለማህበረሰቡ ጥራት ያለውን አገለግሎት እንዲሰጡ ለማገዝ ቢሮው አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል ብለዋል። በክልሉ የጤና አገለግሎቶችን ይበልጥ ለማጎልበትና ተደራሽነትን ለማስፋት ሁሉም የባለድርሻ አካላት ሊተጉ እንደሚገባ ኃላፊው አስገንዝበዋል። ተሽከርካሪዎቹ የእናቶችንና…

Read More

የፍትህ ዘርፋን የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የህብረተሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት በማክበር የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ይገባል-ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የትራንስፎርሜሽን ሪፎርም እና የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የፍትህ ሪፎርም ስራ ሀገራዊ የለውጥ ሂደትን ተከትሎ የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጀመረ እና ውጤት እየተመዘገበበት ያለ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል…

Read More

ህገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ድጂታል የስነ ልኬት ስራዎችን እውን ማድረግ ይገባል። አቶ ተመስገን ከበደ።

በነዳጅ መስፈሪያ መሳሪያዎች ምርመራ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ ለባለድርሻ አካላት እየተሰጠ ነው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ በነዳጅ መስፈሪያ መሳሪያዎች ምርመራ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት እየሰጠ ነው። በዚሁ ስልጠና ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ህገ_ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ድጂታል የስነ _ልኬት ስራዎችን እውን ማድረግ ይገባል…

Read More

ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በቦንጋ ብዝሃ ዋና ከተማ ለሚነገቡ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤትና የክልል ተቋማት ቢሮ ህንጻዎች ግንባታ መሠረተ ድንጋይ አስቀመጡ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በቦንጋ ብዝሃ ዋና ከተማ ለሚነገቡ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና የክልል ተቋማት ቢሮ ህንጻዎች ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል። የመሠረተ ድንጋይ ማስቀመጥ ሥነሥርዓት ላይ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ እንዳሉት፤ በቦንጋ ብዝሃ ዋና ከተማ የሚገነባው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ሌሎች የክልል…

Read More

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከኮንታ ዞን የፊት አመራሮች ጋር በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባራት ዙሪያ ምክክር አድርጓል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኮንታ ዞን በኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ሥራዎች ምልከታና ግምገማ አድርጓል። የድጋፍና ክትትል ቡድኑ የዞን ማዕከል፣ የኤላ ሀንቻኖ እና የጪዳ ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ስራዎችን ተመልክቶ ግብረ መልስ ሰጥቷል። የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ጎበና በተቋሙ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን መነሻ ሪፖርት አቅርበዋል ። የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የሚያደርገው…

Read More

ቢሮው የአሰሪና ሠራተኛ ዘርፍ የአማካሪ ቦርድ ምሥረታ አካሄደ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥራ ክህሎት ቢሮ፤ የአሰሪና ሠራተኛ ዘርፍ የአማካሪ ቦርድ ምሥረታ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። ከአሰሪ፣ ከሠራተኛ እና ከመንግሥት ወገን የተወጣጡ 15 አባላት ያሉት የአማካሪ ቦርድ ተሰይመው በጉባኤው ፊት ቃሌ-መሀል ፈጽመዋል። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቢሮው ምክትልና የአሰሪና ሠራተኛ ዘርፍ ኃላፊ ተክሌአብ ቡሎ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ የአማካሪ ቦርድ መመሥረት በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሚፈጠሩ ችግሮች…

Read More

በሌማት ትሩፋት ስራዎች አስደናቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በሌማት ትሩፋት ስራዎች አስደናቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ። የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በተመለከተ በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ እጅግ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል። አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን አንስተዋል። በእንቁላል፣ በወተት፣ በስጋ ምርት…

Read More

በክልሉ ያሉትን ፀጋዎች በተገቢው በማልማት ከተረጂነት ለመላቀቅ የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ በሙሉ አቅም መረባረብ ያስፈልጋል፦አቶ ፍቅሬ አማን

በክልሉ ያሉትን ፀጋዎች በተገቢው በማልማት ከተረጂነት ለመላቀቅ የሚደረገውን ጥረት ውጤታማ ለማድረግ መረባረብ ያስፈልጋል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ ከተረጂነት መላቀቅና የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ በሚል መሪ ሀሳብ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄ ይገኛል ። በውይይቱ መድረክ የክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደተናገሩት በክልሉ ያሉትን…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል:-

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል:- ባለፉት ስምንት ወራት በዋና ዋና የኢኮኖሚ አመላካቾች ታላላቅ ስኬቶች ተመዝግበዋል፣ በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ይህን ስኬት ማጠናከር ከተቻለ ኢትዮጵያ በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ነጥብ 4 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች፣ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ ችግሮች ቢያጋጥሙም ባለፈው ዓመት…

Read More

በህዝብ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አድምጦ ፈጣን ምላሽ በመሰጠት ለህዝበ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ፦አቶ ፍቅሬ አማን

በህዝብ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳድር ጥያቄዎች አድምጦ ፈጣን ምላሽ በመሰጠት ለህዝበ ተጠቃሚነት በቁርጠኝተን መስራት እንደሚገባ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ማዕከል ያደረገ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት በአገልግሎት አስጣጥ ላይ የህዝቡ…

Read More