ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የሠላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችሉ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ
በክልሉ ብዙኅ ዋና ማዕከላት ከሚገነቡ የክልል ተቋማት ሕንጻዎች አንዱ የሆነው በታርጫ ከተማ የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። የመሠረተ ድንጋዩን ያስቀመጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ እየተከናወኑ የሚገኙ የሠላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ ይገኛሉ ብለዋል። ከዚህ ቀደም የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እያስነሱ የሚገኙትን ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶትን በማጠናቀቅና በማስመረቅ እንዲሁም አዳዲሶችንም…
