የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በክልል ደረጃ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አባላት ያለው የወንጀል መከላከል ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት አቋቋመ
በመድረኩ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዎኖ እንደተናገሩት ዛሬ የሚንመሰርተው ክልል አቀፍ ገለልተኛ የወንጀል መከላከል አማካሪ ምክር ቤት ወንጀልን በተደረጀና በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል ትልቅ አቅም አለው ብለዋል፡፡ በክልሉ ገለልተኛ የአማካሪ ምክር ቤት መመስረት ያሰፈለገበት ዋና ምክንያት ወንጀል የመከላከሉ ስራ ሁላንታናዊ የዜጎች ተሳትፎ ስለሚያስፈልግና አንዱ የዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥበት በመሆኑ ነውብለዋል። ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ከፖሊስ እና…
