ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያዊያን በላብና በደማቸው ያጸኑት የወል ቅርስ ነው:- ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መላው ኢትዮጵያዊያን ተባብረው በላብና በደማቸው ያፀኑት የወል ቅርስ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቅን አስመልከተው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በቦንጋ ከተማ የተካሄደው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በተለያዩ ትዕይንቶች ታጅቦ በስኬት ተጠናቋል። በህዝባዊ ሰልፉ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ…
