በምዕራብ ኦሞ ዞን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በጋችት ወረዳ በይፋ ተጀመረ
በምዕራብ ኦሞ ዞን የዘንድሮው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በጋችት ወረዳ ቤሩ ቀበሌ የክልል እና የዞን የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዞናዊ ማስጀመሪያ በዛሬ በይፋ ተጀምሯል። የተፋሰስ ልማት ሥራው “የአፈር ጥበቃ ስራችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ሃሳብ በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች ላይ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። የክልል እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ የወረዳ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተፋሰስ ስራዎችን አስጀምረዋል።…
