Trendings

የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ እንዲዘጋጅ እየተደረገ ነው

የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ስርዓተ ትምህርቱን መሰረት ያደረገና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ እንዲዘጋጅ እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለጸ። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ስታንደርድ ማስጠበቅ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ የክልሎችና የከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ተወካዮች በተገኙበት በአዳማ እየተካሄደ ነው። የመድረኩ ላይ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ…

Read More

ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል – ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር)

ሀገራዊ የሪፎርም ስራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ መገናኛ ብዙሃን የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) አስገነዘቡ። “ሚዲያ ለብሔራዊ ትርክትና ሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለመገናኛ ብዙሃን አመራሮችና ባለሙያዎች ለሶስት ቀናት ሥልጠና ተሰጥቷል። በሥልጠናው የትርክት እመርታ ከታሪካዊ ስብራት ወደ ሀገራዊ ምልዐት፤ እመርታ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ብልጽግና እና የፖለቲካ እመርታ…

Read More

ለመልካም አስተዳደር ችግር መፈጠር መንስኤ የሚሆኑ አካላትን የማጥራት ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ሆነው ለመልካም አስተዳደር ችግር መፈጠር መንስኤ የሚሆኑ አካላትን የማጥራት ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን በስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። የምክር ቤት አባላቱ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊያና ፖለቲካዊ መስኮች እንዲሁም ወቅታዊ ጥያቄዎችን የተመለከቱ ያቀረቡ ሲሆን…

Read More

በዳውሮ ዞን የሚገኘው የድንጋይ ከሰል ፋብሪካ ለኢንቨስትመንት በር ከፋች መሆኑ ተገለጸ

በዳውሮ ዞን ባለፈው ጥር ወር ተመርቆ ወደ ሥራ የገባው የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ለአካባቢው የኢንቨስትመን ፍሰት በር ከፋች መሆኑ ተገልጿል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የኢቲ-ማዕድን ልማት አክሲዮን ማኅበር የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ለበርካታ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠሩንም የዳውሮ ዞን ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ አስታውቋል። የመምሪያው ኃላፊ ኃይሌ ዱባለ የድንጋይ ከሰል ግብዓት…

Read More

ታሪካዊ የባሕር በር መብታችንን ለማረጋገጥ የበኩላችንን እንወጣለን፡- ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማኅበር

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማኅበር ወቅታዊ በሆነው የሀገሪቱ የባሕር በር አጀንዳ ላይ የፓናል ውይይት አካሄደ። በውይይቱ ላይ የማኅበሩ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ብርሃኑ አማረ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ የባሕር በር ጉዳይ ሀገራዊ አጀንዳ እንዲሆን በማድረጋቸው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል። “ኢትዮጵያና ቀይ ባሕር ተነጣጥለው አያውቁም” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በታሪክ አጋጣሚ…

Read More

“ከኤርትራ ጋር ያለው ቅራኔ የጀመረው ከቀይ ባሕር ጥያቄ በፊት ነው” — ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ስላለው ወቅታዊ ግንኙነት ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ችግር መነሻ የቀይ ባሕር ጥያቄ ሳይሆን፣ ኤርትራ ሀገር ሆና ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ታሪካዊ ሂደት መሆኑን ገልጸዋል። በለውጡ ማግስት በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው የዓመታት ችግር እንዲፈታ መንግሥታቸው ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም፣ ሂደቱ በተፈለገው ልክ…

Read More

ኅብራችን ለሰላማችን – የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት

ኅብረ ብዙ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለኅብር ቀን በሰላም አደረሳችሁ! ጳጉሜን 4 የኅብር ቀን “ኅብራችን ለሰላማችን” በሚል መሪ መልዕክት ተከብሮ ይውላል፡፡ በእርግጥም የኅብር ቀን ኢትዮጵያውያን ዓመቱን ሙሉ ልናከብረዉ የሚገባ ነው፤ ኅብራችን ብዙ ነውና፡፡ በብሔር፣ በቋንቋ፣ በአመለካከት፣ በመልክዓ ምድር፣ በአመጋገብ፣ በአኗኗር ዘይቤ፣ በአለባበስ ወ.ዘ.ተ፡፡ ኅብራዊነታችን ሰፊ ነው፡፡ ይህ ኅብራችን ደግሞ ውበታችን፣ ሀብታችን፣ የደስታና የጥንካሬያችን ምንጭ ነው፡፡…

Read More

ምቹ የእናቶች ማቆያ በማዘጋጀትና ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት በመስጠት የእናቶችና ህፃናት ሞት መቅረፍ ይገባል፦ አቶ ኃይለ ዘውዴaxda

‎ ‎የክልሉ ጤና ቢሮ እናቶች፤ ህፃናት አፍላ ወጣቶች ጤና እና ስነ-ምግብ ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም እና የ2018 ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ‎ ‎በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የጤና ተቋማትን ለማስፋፋት በሰጠው ትኩረት አዳዲስ ጤና ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። ‎ ‎በክልሉ…

Read More

ከውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደር እየተዘጋጁ መሆኑን ባንኮች ገለጹ

ከውጭ ከሚገቡ ባንኮች ጋር ለመወዳደር አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የሀገር ውስጥ ባንኮች አስታወቁ፡፡ የውጭ ባንኮች በሀገር ውስጥ በዘርፉ እንዲሰማሩ የሚፈቅደው የባንክ ሥራ አዋጅ በቅርቡ መጽደቁ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም ፋና ዲጂታል ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ጋር በዘርፉ ለመወዳደርና አቅማቸውን ለማሳደግ የሀገር ውስጥ ባንኮች ምን እየሰሩ ነው ሲል ጠይቋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ÷ የውጭ ባንኮች በሀገር…

Read More

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 50 ሚሊየን 514 ሺህ በላይ መራጮች ተመዝግበዋል፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 50 ሚሊየን 514 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ። የሰባተኛው ጠቅላላ የመራጮች ምዝገባ ትናንት ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠናቋል። ዜጎች በምርጫዬ የሞባይል መተግበሪያ የዲጂታል አማራጭና በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የመራጮች ምዝገባ አከናውነዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ ቦርዱ…

Read More