ምክር ቤቱ 13 አቤቱታዎች የሕገመንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል ሲል ውሳኔ አሳለፈ
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከቀረቡለት አቤቱታዎች ውስጥ 13ቱ የሕገመንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል ሲል ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ምክር ቤቱ 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል። በጉባኤው የሕገመንግሥት ትርጉምና የውሳኔ አፈፃፀም ክትትል ቋሚ ኮሚቴ መርምሮ ባቀረባቸው የውሳኔ ሃሳቦች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም በምክር ቤቱ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል…
