Trendings

Getenesh Gebeyehu

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ አርአያ የሚሆን ሥራ እያከናወነች ነው – የአፍሪካ ቻይና ፖሊሲና ምርምር ማዕከል

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ለአፍሪካ ሀገራት አርአያ የሚሆን ሥራ እያከናወነች ነው አለ የአፍሪካ ቻይና ፖሊሲና ምርምር ማዕከል፡፡ የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ፖል ፍሪምፖንግ በ2025 የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ጉባዔ ላይ እንዳሉት÷ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ምሕዳር ግንባር ቀደም መሆን የሚያስችሉ ጠንካራ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲዎችን እየተገበረች ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዘርፉ ጠንካራ ፖሊሲን በመቅረጽ ቀጣይነት ያለው ሥራ እያከናወነች ነው ያሉት…

Read More

ሰራዊቱ አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል – ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

ሰራዊቱ በመኖሪያ ካምፕ እና በግዳጅ ቀጣናው አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወቃል። የመከላከያ ሰራዊት የዘንድሮ የአረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመከላከያ ሚኒስቴር…

Read More

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አስጀመሩ

በሀገር አቀፍ በ2017 ዓ.ም በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አካል በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጀምሯል። በመርሐግብሩ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፤ የዋና ጽ/ቤት፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አመራሮችና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል። የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአረንጓዴ…

Read More

የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነው።

ከሀምሌ 07/2017 ዓ.ም ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ይገኛል። በዕለቱ የፓርቲ ሰነዶችና መመሪያዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ነው። የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ ሪፖርት፤ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። #prosperity

Read More

በዞኑ 364 የግል ባለሀብቶች በተለያዩ የእንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራታቸው ተገለጸ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን 364 የግል ባለሀብቶች በተለያዩ የእንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራታቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ገልጸዋል። ኢንቨስትመንት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት እና የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት የዞኑ ዋና አሰተዳዳሪ ጨምሮ መግለፃቸውን የካፋ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል። የካፋ ዞን ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ የኢንቨስትመንት ምክክር ፎረም ቦንጋ ከተማ መካሄድ…

Read More

ኢትዮጵያ በፖሊሲ የታገዙ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የመቋቋም ተሞክሮዋን የምታጋራበት መድረክ

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ኢትዮጵያ በፖሊሲ የታገዙ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን የመቋቋም ተሞክሮዋን የምታጋራበት መድረክ ይሆናል አለ። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመሆን ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታስተናግዳለች። ጉባኤውን አስመልክቶ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ ፋውንዴሽን፣ ለጋሽ ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደች ነው። የፕላንና ልማት ሚኒስትር…

Read More

ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ ጥሩ አፈፃፀም ካላቸው ሀገራት መካከል ነች

25ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የፋይናንስ ሚኒስትሮች ስብሰባ በኬኒያ ናይሮቢ በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ የተሳተፉ ሚኒስትሮች ዲጂታል ትስስርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ በፈረንጆቹ 2023 ስለፀደቀው የዲጂታል ውህደት እና የፖሊሲ ማዕቀፍ ሚኒስትሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህም ሀገራት ጥሩ አፈጻጸም በማስመዝገብ ላይ መሆናቸው የተመላከተ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ጥሩ አፈፃፀም ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ነች ተብሏል፡፡ በምክክሩ የተሳተፉት የገንዘብ ሚኒስትር…

Read More

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባከናወናቸው የሪፎርም ስራዎች ኢትዮጵያን የሚመጥን ዘመናዊ አሰራር መገንባቱን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ገለጹ

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከክልል መዝጋቢ እና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ያተኮረ ጉባኤ እያካሄደ ነው። በመድረኩ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፣ የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አመራር እና አባላት እንዲሁም ሌሎች…

Read More

በ 6 ዓመት ግንባታ ገና 32 በመቶ ላይ የሚገኘው የቴፒ ሺሽንዳ መንገድ

‎ ‎ከቴፒ ሺሽንዳ በመገንባት ላይ ያለው የአስፓልት መንገድ በመጓተቱ ለእንግልት ተዳርገናል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ‎ ‎ከ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዞለት ግንባታው የተጀመረው 77 ኪ.ሜ የሚረዝመው የሺሺንዳ ቴፒ አስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ተቋርጦ መቅረቱ ለእንግልት እየዳረጋቸው መሆኑን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን የቢጣ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ። ‎ ‎የመንገድ ሥራው ስድስት…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት አመት የአስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቱ የክልሉን አስፈፃሚ አካላት ተግባር በየደረጃው በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል። አክለውም የመድረኩን አላማ በማስረዳት፣ የአፈፃፀም ሪፖርቱ የምክር ቤቱን ደንብ በጠበቀ መልኩ እንዲቀርብ አሳስበው መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል። በዚህም መሰረት ህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር፣ ግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች፣ በጀትና…

Read More