የወባ ስርጭትን መከላከልና መቆጣጠር ስራ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ ይጠይቃል ተባለ
የሸካ ዞን ጤና መምሪያ የ2017 የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ተግባር ያለበት ደረጃና የቀጣይ ተግባራት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቴፒ ከተማ ውይይት አካሂዷል። የውይይት መድረኩን የመሩት የሸካ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ በላቸው ጋራ እንደተናገሩት የወባ ስርጭትን መከላከልና መቆጣጠር ስራ የሁሉንም ህብረተሰብ ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል። በየደረጃው የሚገኘው የፓርቲና የመንግስት አመራር…
