በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተቀመጡ ስትራቴጅዎችን በመፈጸም አምራቹና ሸማቹን ቀጥታ በማገናኘት ገበያን ለማረጋጋትና የኑሮ ውድነት ለመቀነስ ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ።
ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት ”ሀገራዊ የንግድ ሳምንት አከባበር አስመልክቶ የንግድና ኢንቨስትመንት ሴክተር የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምስረታ ጀምሮ የእስካሁኑ ጉዞ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ዓላማ ያደረገ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ በንግድ እና እንቨስትመንት ዘርፍ እስካሁን ተከናወነዉ የተመዘገቡ ውጤቶችን ማጠናከር እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ማረም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ምክክር…
