ወቅታዊ፣ ትክክለኛና ግልፅ መረጃ በፍጥነትና በአስተማማኝ ሁኔታ በመስጠት ቀውስን መቀነስ እንደሚገባ ተገለጸ
የድህረ እውነት ዘመንን በእውነትና በዕውቀት” በሚል መሪ ቃል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፤ ለህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ባለሙያዎችና አመራሮች በቦንጋ ከተማ እየተሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠና እየቀጠለ ይገኛል። የቀውስ ጊዜ ኮሙኒኬሽን እና የመረጃ ማጣራት ሂደት ላይ የስልጠና ሰነድ በኢዜአ የሚዲያ ክትትልና መረጃ ማጣራት ዳይረክቶረት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ አብዱ አሊ ለተሳታፊዎች እየቀረበ ይገኛል። ቀውስ በተፈጥሮም ሆነ በሰው…
