ኢትዮጵያ 2ኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታስተናግዳለች – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር 2ኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንደምታስተናግድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
በአካቢው የንጹህ መጠጥ ውሃ ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን በሸኮ ወረዳ የግዝ መሬት- ሺም የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ከዘላቂ የልማት ድርጅት ፕሮጀክት (SDG) በተገኘው 34 ነጥብ 7 ሚለየን ብር የበጀት ድጋፍ የተገነባው ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ። ያነጋገርናቸው የግዝ መሬትና ሺሚ ቀበሌ ነዋሪዎች በቀበሌው የንጹህ ውሃ ተመርቆ አገልግሎት ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በፊት በቂ የሆነ…
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?
ባለፉት ተከታታይ ሳምንታት ‘’የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ምን ያህል ያውቃሉ?’’ በሚል አምድ ሥር አጠቃላይ የክልላችንን ገጽታ፣ የምዕራብ ኦሞ፣ የካፋ፣ የዳዉሮ፣ የቤንች ሸኮ እና የሸካ ዞኖችን አጠቃላይ ገጽታ የሚያሳዩ ጽሁፎችን እንደየቅደምተከተላቸው ለውድ አንባቢያን አጋርተናል፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ከክልላችን ዞኖች አንዱ የሆነውን የኮንታ ዞንን እንቃኛለን፡፡ መልካም ንባብ!የኮንታ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተደራጁ ስድስት ዞኖች…
ለፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ በሚመደቡ ሀብቶች ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ተደማሪ ሀብት ለማግኘት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ
ክልላዊ የልማት ክፍተቶችን ለመቅረፍ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች የሚመጡ ሀብቶችን ከዓለም ባንክ ጋር በተገባው ስምምነት መሰረት በተገቢው ስራ ላይ ማዋል እንደሚጠበቅም ተገልጿል ፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ የካልም ፕሮጀክት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተደርጓል ፡፡ በአፈጻጸም ግምገማው የተገኙት በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የመንግስታት ትብብር ሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ኃላፊ…
የመንግስት ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍናን ለማሳደግ የሚያስችል የሪፎርም ትግበራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ በሪፎርም የሚካተቱ የክልል ቢሮዎች፣ ለዞን መምሪያ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲና በክልሉ ፍኖተ ካርታ ላይ የተዘጋጀ ስልጠና በቦንጋ ከተማ እተሰጠ ይገኛል፡፡ የቢሮዉ ሃላፊ አቶ አስራት አዳሮ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸዉ፣የመንግስት የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ዓላማ የመንግስት ተቋማትን ቅልጥፍናና ዉጤታማነት፣ግልጽነት፣እና ተጠያቂነት በማሻሻል ቀልጣፋ ዉጤታማ…
በክልሉ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበጎ ፈቃድ ስታንዳርድ እና ትመና ላይ ለዞን አመራሮች እና ባለሙያዎች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል። በዘንድሮው የክረምት ወጣቶች በጎ ፍቃድ አግልግሎት ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጎ ፍቃድ አግልግሎት ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን ነው የክልሉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ…
“ሪፖርታዥ”
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ለሀገሪቱ ፖልሲ ቀረፃ ግብዓት ከመሆኑም ባሻገር የዜጎችን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ጉልህ ድርሻ አለው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ በሀገር ደረጃ በአዋጅ 760/2004 ፤ በተሻሻለው 1049/2009 ተደንግገው ለሰብዓዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ መብቶች እንድሁም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃምነትን በቋሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል ህጋዊ መረጃ ለዜጎችና ለመንግስት ለማቅረብ የሚሰራ ዘርፍ ነው፡፡ የሲቪል መረጃ ምዝገባ ከየትኛውም መረጃ በላይ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ከፌደራል ጀምሮ…
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
ከተለያዩ ዘርፎች ጋር የምናደርገውን ውይይት በመቀጠል ዛሬ ከመላው ኢትዮጵያ ከተወጣጡ መምህራን ጋር የሚነሱ ጉዳዮችን በማዳመጥ እና ለእቅድ ስራችን ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦችን በመውሰድ ውይይት አድርገናል
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ ርጥበት ይኖራቸዋል – ኢንስቲትዩቱ
በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሻለ የርጥበት ሁኔታ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ በሚቀጥሉት አስር ቀናት የሚኖረውን የአየር ትንበያ አስመልክቶ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በሚቀጥሉት ቀናት የሚኖረው የአየር ሁኔታ ለእርሻ ስራ እንቅስቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው አመላክቷል። ከዚህም ጋር ተያይዞ በምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚጠበቀው ከባድ ዝናብ ለወቅቱ የእርሻ ስራ…
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ኤምባሲ የልዑካን ቡድን ጋር መከሩ ።
የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ መልዕክተኞች በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ድንበር አከባቢ የሚፈጠሩ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ ምክክር በቦንጋ ከተማ አካሂዷል። በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል የቆየውን ታሪካዊ ወዳጅነት በማስቀጠል የህዝብ ለህዝብ ግኑኝነት እና ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ትስስር በማስቀጠል እንዳለበት በውይይቱ ተመላክቷል። ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ሪፑብሊክ ጋር ሰፊ ድንበር የሚጋራ በመኾኑ፥ በድንበር አከባቢ የሚከሰቱ ችግሮችን በዘላቂነት…
