የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ለቦንጋ የመደመር ትውልድ ቤተ-መጻሕፍት ላይብራሪ የኮምፒውተር ድጋፍ አደረገ።
ኮርፖሬሽኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ለተገነባውን ቤተ-መጻሕፍት የዲጂታል ላይብራሪ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ዋጋ ግምት ያላቸዉን 20 ኮምፒዩተሮችን ድጋፍ አድርጓል። በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ኮርፖሬሽኑ የክልሉን ግብርና ለማዘመን የግብርና ግብዓት እና የሜካናይዜሽን አቅርቦት ለማሳለጥ ማዕከል…
