የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየም ለህዝብ ክፍት ሆነ
እድሳት ተደርጎለት ላለፉት 4 ወራት በሙከራ ስራ ላይ የቆየው የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ተደርጓል፡፡ ቤተመንግስቱ ጥንታዊ ተሽከርካሪዎችና መካነ እንስሳትን ጨምሮ በውስጡ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ሲሆን፥ ደረጃቸውን የጠበቁ ሬስቶራንቶችና ስፓዎች ይገኙበታል፡፡ ሙዚየሙ ክፍት መደረጉን አስመልክተው የብሔራዊ ቤተመንግስት ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምትኩ ደሬሳ በሰጡት መግለጫ፥ ቤተመንግስቱ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ለማላቀቅ ትልቅ ሚና እንዳለው አንስተዋል፡፡…
