Trendings

Getenesh Gebeyehu

በአዋጆቹ ዙሪያ የሚሰጠው ስልጠና ቀጥተኛ ያልሆነ ታክስን አሟጦ ለመሰብሰብ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው – ወ/ሮ ህይወት አሰግድ

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ የደንበኞች አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ የስራ ክፍል ዘርፍ በክልሉ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 34/2016፣ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 36/2016 እንዲሁም በገጠር መሬት መጠቀሚያ ኪራይ እና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 28/2016 ዙሪያ በዘርፉ ውስጥ ላሉ አዳዲስ ባለሙያዎች በሚዛን ከተማ ስልጠና እየሠጠ ነው። በስልጠናው የቢሮው ምክትል ኃላፊና የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ…

Read More

ለሀገራዊ ምርት ዕድገት የተሻሻሉ የቡናና ቅመማቅመም ፓኬጆች እሰተዋጽኦ ጉልህ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮዽያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ከምርምር ማዕከላት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው በተሻሻሉ የቡናና ቅመማቅመም ፓኬጆች ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና መድረክ በሚዛን አማን ከተማ ጀምረዋል። መድረኩን ያስጀመሩት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አማካሪና የግብርና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ መላኩ የኢትዮዽያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንን ለሀገራችን ኢኮኖሚ ፈር ቀዳጅ ለሆነው የቡናና ሻይ ዘርፍ ዙሪያ ስልጠና በክልላችን እንዲዘጋጅ ስላደረገ አመስግነዋል። የደቡብ ምዕራብ…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት የክልሉ የአስተዳደር ጉዳዮች ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት የክልሉ የአስተዳደር ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ይገኛል። በግምገማዉ መድረኩ እንደክልል በሩብ ዓመቱ ታቅደው በጥንካሬ የተከናወኑ ተግባራት እንዲጠናከርና ድክመቶችን በጋራ በመገምገም እንዲሁም ቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል። የክልሉ የአስተዳደር ተቋማት ማለትም ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፣…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የመሠረተ ልማት ክላስተር ተቋማት የ9 ወራት የተግባር አፈፃፀም ግምገማ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዋ ሳፒ እንደገለፁት እያደገ የመጣውን የህዝብ የመሰረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት የጋራ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይገባል ብለዋል ። በመሰረተ ልማት ክላስተር ሥር ያሉ ተቋማት በዕቅድ አፈፃፀም ያለውን ጥንካሬና ጉድለቶች በመለየት የጋራ አረዳድ በመያዝ ለቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም መዘጋጀት…

Read More

njjjሀገራዊ ልማት የሁሉንም ርብርብ ስለሚጠይቅ ምልዓተ ሕዝቡን አስገንዝቦ ማነሣሣት ላይ ሊተኮር ይገባል፦ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ

ሀገራዊ ልማት እና ሁለንተናዊ ዕድገት ማረጋገጥ የሚቻለዉ ቀጣይነት ያለው የምልዓተ ሕዝቡ ተሳትፎ በመሆኑ ሀገራዊ ትልሞችን እና የመዳረሻ ግቦችን ማስገንዘብ ላይ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ እንዲያተኩር የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ “ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለኢትዮጵያ መንሰራራት” በሚል መሪ መልእክት ለክልል እና ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በአዲስአበባ እየተሰጠ ባለው ሥልጠና…

Read More

ባለፉት 9 ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች ሳያዘናጉን ለበለጠ ከፍታ ሊያነሳሱን ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ ተጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በግምገማው የሚቀጥሉትን 3 ወራት ሥራዎቻችንን እቅድ ለማጠናከር የሚረዱ ውይይቶችን እናካሂዳለን ብለዋል። እስካሁን ያሳካነው የሥራ ውጤት ሰፊ ቢሆንም ስኬታችን ሳያዘናጋን ለበለጠ ከፍታ የሚያነሳሳን ሊሆን ይገባል ነው ያሉት ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Read More

አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ድጋፍ ማድረግ ይገባል – ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)

አምራች ኢንዱስትሪዎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ገለፁ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ነው፡፡ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በማቃለል የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ሊደገፉ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ማነቆ…

Read More

የኮሙኒኬሽን ሥራን ዓላማ ተኮር ማድረግ እንደሚገባ ተመላከተ

ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ የኮሙኒኬሽን ሥራችንን ዓላማ ተኮር ማድረግ አለብን ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶር) አስገነዘቡ፡፡ “ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለኢትዮጵያ መንሠራራት” በሚል መሪ ሐሳብ ለክልል እና ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው የዐቅም ግንባታ ስልጠና እንደቀጠለ ነው፡፡ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የበይነ-መረብ ዐውዱ የመረጃ ፍሠቱን ከአንድ ወደ ባለብዙ…

Read More

በኮንታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት “የአስተሳሰብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በዞን ማዕከል ዞናዊ የአመራር አቅም ግንባታ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ሀገራዊ፣ ክልላዊና ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታ የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ በ2 ቡድን ውይይት የሚደረግ ሲሆን አመራሩ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ራሱን እንዲያዘጋጅ ለማስቻል ያለመ ስለመሆኑ ተመላክቷል። በመድረኩ የዞኑን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙን ጨምሮ የዞን አመራሮች፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Read More

ዞናዊ ነበራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ አጠቃላይ የዞን አመራርና ወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታን መሠረት ያደረገ አጠቃላይ የዞን አመራርና የወረዳ እና ከተማ አስዳደር አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ፥ የመድረኩ ዓላማ ቀደም ሲል በተሰጡ የአመራር መድረኮች የተገኙ አቅሞችን በማቀናጀትና በአመራር መካከል የተግባር አንድነትን በመፍጠር የህዝብ የልማት አቅሞችን…

Read More