በግማሽ ዓመቱ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል፡፡ የክልሉ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2017 ግማሽ ዓመት የመንግሥትና የፓርቲ የዕቅድ አፈጻጸም የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እና የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ተገምግሟል። በግምገማው ላይ ባለፉት 6 ወራት በክልላችን በተሰሩ የልማት ስራዎች ተከናውነው የተሻሉ አፈጻጸሞች መኖራቸውን ያህል ትኩረት የሚሹና በቀጣይ የሚሰሩ ጉዳዮች መኖራቸውን የመድረኩ ተሳታፊ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል ። በመድረኩ…
