ስፖርት ለአካላዊ ብቃትና ለአዕምሮ ጤንነት የጎላ ሚና እንዳለው የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ተናገሩ::
መላው የካፋ ዞን እግር ኳስ ክለቦች ጨዋታ በቦንጋ ሁለገብ ስታዲየም ተጀመረ። የ2016 ዓ.ም መላው የካፋ ዞን የእግር ኳስ ክለቦች ጨዋታ በቦንጋ ሁለገብ ስታዲየም የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ጀምሯል። የሠላም ተምሳለት፣የአረንጓዴ ፈርጥ እና የክልሉ የፖለቲካና የአስተዳደር መቀመጫ ቦንጋ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የቦንጋ ከተማ ከንቲባ አቶ አስማማው…
