Trendings

Getenesh Gebeyehu

ስታርት አፕ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችሉ ናቸው፦የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር::

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ስታርትአፖች መበራከት እንደሚገባቸው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ስታርትአፕን ለማበረታታት እየተሞከረ መሆኑ በመጥቀስ ቀጣይነት እንዲኖራቸው እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡ የስታርትአፕ ሀሳብ ያላቸው ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ተዘጋጅተው የሚመጡባቸው ምቹ መድረኮች እንዲኖሩ እየተሰራ ይገኛል የሚሉት ኃላፊው…

Read More

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጄንሲ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው::

14ኛው ዓለም አቀፉ የታዳሽ ኃይል ኤጄንሲ ጉባዔ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቡ ዳቢ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡ በጉባዔው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡ በጉባኤው ከታዳሽ ኃይል እና የአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በርካታ ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ…

Read More

የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ማተኮር እንደሚገባ ተገለጸ::

በስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ የልዑካን ቡድን በቤንች ሸኮ ዞን የተለያዩ የስራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኃላ ከሚመለከታቸው ጋር የጋራ ውይይት አካሂደዋል። የኢፌዲሪ ስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት በሥራ ክህሎት ላይ ያሉ አዳዲስ እሳቤዎችን በማስረጽ እንደ ሀገር የተጀመሩ ሥራዎችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። ክልሉ ያለውን የአካባቢ ፀጋ በመለየትና በማልማት…

Read More

የሕብረት ሥራ ማህበራትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሪፎርም ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ::

የሕብረት ሥራ ማህበራትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሪፎርም ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ሕብረት ሥራ ኤጄንሲ ገለጸ። በአንድ ሺህ መሠረታዊ ማህበራት ላይ ሪፎርም እንደሚደረግ ተጠቁሟል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 2069 መሠረታዊ ማህበራትና 21 ዩኒየኖች ይገኛሉ። የሪፎርሙ ዓላማ የሕብረት ስራ ማህበራትን ተወዳዳሪ ለማድረግ፣ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር፣ የፋይናንስ አቅማቸውን ለማሳደግ፣ አሰራርን ለማሻሻልና የአባላትን…

Read More

በክልሉ በሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ለማድረግና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ተባለ::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ዲጂታል የማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን በሚዛን አማን ከተማ በይፋ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማት ማናጅመንት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ እንደገለጹት በክልሉ ከሚገኙ ብዘሀ ከተሞች አንዷ በሆነችው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ለመዘርጋት…

Read More

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ‘አስተውሎት’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ፊልም አስመረቀ::

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ‘አስተውሎት’ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውን ፊልም አስመርቋል ፡፡ ፊልሙ ትኩረቱን ኢንስቲትዩቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ባከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ አድርጓል፡፡ ፊልሙን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከሰውኛ ፕሮዳክሽን እና ኢንተርቴይንመንት ጋር በመሆን በጋራ አዘጋጅተውታል። በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ…

Read More

በኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ ልዑክ የበበቃ ኮፊስቴት የልማት ስራዎችን ጎበኘ::

ከኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከክልሉ ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ መስሪያ ቤቶች እና የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በቤንች ሸኮ ዞን የሚገኘውን የበበቃ ቡና ልማት፣ የቻንቹ ሙዝ ክላስተርን ጨምሮ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል። በሚድሮክ የኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር በኢትዮ አግሪ-ሴፍት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የበበቃ ኮፊስቴት ከ2 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች ቋሚና ከ10 ሺህ በላይ ጊዜያዊ የሥራ ዕድል…

Read More

በዞኑ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ተግባራት በሙሉ አቅም ተፈፃሚ ለማድረግ በቀሪ ወራት ሁሉ ዐቀፍ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።

የኮንታ ዞን አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ተካሂዷል። የአፈፃፀም ግምገማው በአስተዳደራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና መሠረተ-ልማት ዘርፎች በመከፋፈል ነው የተገመገመው በአፈፃፀም ግምገማው ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ነጋ አበራ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተጣለባቸውን ተልዕኮ ለመወጣት ዕቅዳቸውንና አፈፃፀማቸውን እየፈተሹ ለውጤታማነት መትጋት እንደሚገባ አስረድተዋል። የህብረተሰቡን ሰላም፣ ፀጥታና ደህንነት ከማስጠበቅ ጀምሮ ፍትሃዊና…

Read More

የባታ ካሹ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ስራ 55 በመቶ መድረሱ ተገለጸ::

በሼይ ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ታደሰ ኒሳብ የተመራው የሀይማኖት አባቶች፣ የቀበሌ ተወካዮች፣ የነጋዴ ማህብረሰቦች፣ የሞዴል አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ህንፃ እና የባታ ካሹ ወንዝ ድልድይ ግንባታ ሂደትን ጉብኝት አድርገዋል። ድልድዩ በህብረተሰብ ተሳትፎ በ25 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ መሆኑን ያብራሩት የሼይ ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ኒሳብ ስራው…

Read More

በሸገር ከተማ አስተዳደር በከባድ የማታለል ወንጀል ሲፈለግ የነበረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኝኙነትና ኮሚንኬሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ በሸገር ከተማ አስተዳደር በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ በተለያዬ አራት ሀሰተኛ ስሞችን በመጠቀም በ15 ግለሰቦች ላይ በከባድ የማታለል ወንጀሎች በመፈፀም ክስ ተመስርቶበት በፖሊስ ሲፈለግ መቆየቱን ፖሊስ ኮሚሽኑ ገልጿል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ተጠርጣሪውን በተገኘበት እንዲያዝ ከፍርድ ቤት መያዣ ጋር በመላካቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ…

Read More