በሚዛን አማን ከተማ በአራት ቀበሌዎች 1 ሺህ 148 ይዞታዎች ወደ ህጋዊ ትግበራ መግባታቸው ተገለጸ ።
በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የሴፍትኔት ፕሮግራሞች እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ዙሪያ ምልከታ ተደርጓል ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር የማታለም ቸኮል በከተማ አስተዳደር ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል። በምልከታው ወቅት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ቤሪ እንደገለጹት በክልሉ ደንብና መመሪያ ወጥቶ በስራ ላይ የሚገኘው ሳይፈቀዱ የተያዙ…
