ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያግዛትን 5ኛ ዙር ድርድር በግንቦት ወር ታካሂዳለች – አቶ ገብረመስቀል ጫላ
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያግዛትን 5ኛ ዙር ድርድር በግንቦት ወር እንደምታካሂድ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ ገለፁ። አቶ ገብረ-መስቀል ጫላ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከ20 ዓመታት በፊት የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እንቅስቃሴ ጀምራለች። ይሁንና በኮቪድ 19 ወረርሽኝና በሌሎች ምክንያቶች ድርድሩ ተቋርጦ እንደነበር የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የጀመረችውን…
