በኢፌዲሪ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ የተመራው የሱፐርቪዥን ልኡካን ቡድን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል።
ሱፐርቪዥን ቡድኑ በተመረጡ 17 የትኩረት መስኮች በተለይም ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ነው በዞኑ ድጋፍና ክትትል ያደረገው። በዚሁ መሠረት የተግባራት አፈፃፀም ያሉበትን ደረጃ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ወርዶ ምልከታ አድርጓል። ልዑኩ በዳውሮ ዞን ኢሠራ ወረዳ አሩሲ አንገላ ቀበሌ በ195 ሄክታር በዘመናዊ መስኖ የለማ የበጋ ስንዴ እንዲሁም በወረዳው የአሩሲ ባላ ቀበሌ በኩታ ገጠም ዜዴ በ72…
