ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢንቨስትመንት ከባቢውን ምቹ ያደረጉ የማሻሻያ ተግባራት ተከናውነዋል
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢንቨስትመንት ከባቢውን መቀየር ያስቻሉ በርካታ ስኬታማ ማሻሻያዎች መከናወናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ዐቅም ለማሳደግ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተነድፎ ዓይነተ-ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከሚያተኩርባቸው ዘርፎች አንዱ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ፍሰት በይበልጥ ማሳደግ መሆኑንም አስረድተዋል። በዚህም የኢንቨስትመንት ምኅዳሩን ለማሻሻል…
