ስኬቶቻችን የሰንደቃችን ከፍታ የሚጨምሩ ናቸው፦ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት እመርታዊ ስኬቶችን እያስመዘገበች የሚመጥናትን ከፍታ እየያዘች ትገኛለች። ለዘመናት የቁጭት እና እንጉርጉሮ ትርክት ምንጭ የነበረዉን ዓባይን ገርታ የኃይል እና ብርሃን ምንጭ አድርጋለች፡፡ በንጋት ኃይቅ በምግብ ሉዓላዊነቷ ላይ ጉልህ ሚና የሚጫወት የዓሣ ምርት ማግኘት ችላለች፤ ዐዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ደሴቶችንና ከተሞችን ፈጥራለች፡፡ የዓባይን የቁጭት ትርክት ወደ ድል እና አሸናፊነት ብስራት ቀይራለች፡፡ ተጨማሪ የኃይል…
በኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃቶችን መመከት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ ነው
በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት እና አስተማማኝ የቴክኖሎጂ ዕድገትን እውን ለማድረግ የሳይበር ደህንነት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ገለጹ። ኃላፊዋ ይህን ያሉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 6ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ባስጀመሩበት መድረክ ነው። 90 ሚሊዮን የስልክ ተጠቃሚዎች እና 50 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ባሉበት ሀገር…
የሰንደቅ ዓላማ ቀን የሀገር ፍቅርና የአንድነት ቃል ኪዳን የሚታደስበት ዕለት ነው – የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት
በመጪው 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔራዊ አንድነትና የሉዓላዊነት ቃል ኪዳን የሚታደስበት ልዩ ዕለት ሆኖ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ። የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በሰጡት መግለጫ፣ ሠንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያን የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ የህዝቦቿን አንድነትና የማይደፈር ሉዓላዊነቷን የሚያመለክት የተቀደሰ አርማ መሆኑን ገልጸዋል። አፈ ጉባዔዉ በመግለጫቸዉ…
የገቢ አሰባሰብን በውጤታማነት መምራት ጠንካራ ሀገር የመገንባት ህልማችንን ለማሳካት ወሳኝ ነው – አቶ አደም ፋራህ
የገቢ አሰባሰብን በውጤታማነት መምራት ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማፋጠን ጠንካራ ሀገር የመገንባት ህልማችንን ለማሳካት ወሳኝ ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለፁ። የገቢዎች ሚኒስቴር ከፌዴራል የክልልና የከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ከመስከረም 29 ቀን 2018 ጀምሮ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሲያካሂድ የቆየውን የውይይት…
የዕቅድ ክትትልና ግምገማ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ያለመ የሥራ ጉብኝት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ተጀመረdcs
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የእቅድ አፈጻጸምና የልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን እና ለማጠናከር ያለመ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ በፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተመራ የፌደራል ልዑክ ቦንጋ ከተማ ገብቷል። የልዑካኑ ጉብኝት ዋና ዓላማ የክልሉን የልማት ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ግልጽ፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ የሚያስችል ዘመናዊ የዲጂታል እቅድ ክትትልና ግምገማ ስርዓትን በተግባር ላይ ለማዋል…
ነዋሪዎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሥራት ከባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ተባለ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከተማ ሴፍትኔት ሥራ ፕሮጀክት(UNSNJP) እና የመንግስት ተዛማጅ ፈንድ(GME) የ2016/17 አፈጻጸም ሪፖርትና የ2017/18 ጠቋሚ ዕቅድ ላይ የክልሉ ስተሪንግ ኮሚቴ በሚዛን አማን ከተማ ውይይት አካሂዷል። የሴፍትኔት ፕሮግራሙ አቅመ ደካሞችን በከተማ ግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በከተማ ቆሻሻ ማፅዳት፣ በአረንጓዴ ልማትና በሌሎች የአካባቢ ልማት ስራዎች ከግንዛቤ እስከ ምርት ድረስ እየደገፈ መሆኑ ተጠቅሷል። መድረኩን የመሩት የክልሉ ከተማ…
