የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የባለሙያዎችን ክህሎት በስልጠና መገንባት ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከክልሉ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ (FSRP) ፕሮግራም ጋር በመተባበር የበጋ መስኖ ስንዴ አመራረት ፓኬጅ ላይ ከዞንና ከወረዳ ለተወጣጡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል፡፡ የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የባለሙያዎችን ክህሎት በስልጠና መገንባት ወሳኝ መሆኑ ተናግረዋል፡፡…
