ኢትዮጵያ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ዕድል የመጀመሪያውን ምርቷን ወደተለያዩ ሀገራት ልትልክ ነው – የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ድርድርን ማጠናቀቋን ተከትሎ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሸቀጦች ዘርፍ የንግድ ትግበራዋን በይፋ እንደምትጀምር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ውሀብረቢ እንደገለጹት ፤ የመጀመርያው የንግድ ልውውጥ በምስራቅና በደቡብ አፍሪካ አገራት ላይ ትኩረት ያደርጋል። ነፃ ንግድ ቀጣና ንግድ ማስጀመሪያው ላይ በኢትዮጵያ አየር…
