በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና በዘርፋ የስራ ዕድል ፈጠራን ለማጠናከር በእንሰሳት ሀብት ልማት ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ ለዞንና ወረዳ የእንስሳት ዘርፍ ሃላፊዎች እና ጤና ባለሙያዎች ክልላዊ የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ማስጀመሪያ እና የእንስሳት ጤና ፓኬጅ ስልጠና መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳት ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ እንሰሳት ጤና ዳይሬክቶሬት ከምግብ ሥርዓት ማጣናከሪያ ኘሮግራም ጋር በመተባበር በተዘጋጀው መድረክ ላይ በቢሮው የእንስሳት እና ዓሳ…
ዜና ሹመት!
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል። በብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅር ያሉት አመራሮች የግምገማና የምዘና መድረክ በጥብቅ ዲስፕሊን በመምራት በክልል ደረጃ አመራሩን መልሶ የማደራጀት ሥራ ተከናዉኗል። የአመራር ስምሪቱ የአመራርን ውጤታማነት፣ ስነ ምግባርን እና ዝግጁነትን መሠረት በማድረግ በጥልቀት የተከናወኑ መሆኑን ተጠቁሟል። አዲስ የተሾሙና የተሸጋሸጉ አመራሮች መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን…
ምቹ የእናቶች ማቆያ በማዘጋጀትና ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት በመስጠት የእናቶችና ህፃናት ሞት መቅረፍ ይገባል፦ አቶ ኃይለ ዘውዴaxda
የክልሉ ጤና ቢሮ እናቶች፤ ህፃናት አፍላ ወጣቶች ጤና እና ስነ-ምግብ ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም እና የ2018 ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የጤና ተቋማትን ለማስፋፋት በሰጠው ትኩረት አዳዲስ ጤና ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል። በክልሉ…
ወጣቶች ሀገራቸውን ለመገንባት ከወትሮ በተሻለ ትጋት እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀረበ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ “የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶችን ያማከለ ንቅናቄ ለነገው ትውልድ ግንባታ ሚና አለው ” በሚል መሪ ሀሳብ ለባለ ድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው። በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ: ሀገራችን ለጀመረችበት የማንሰራራት ጉዞ የሴቶችና ወጣቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቶች ለሀገር ግንባታና…
ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል የፀጥታ ስጋት ተጋላጭነት መቀነስ እንደሚገባ ተገለጸ።
የኢፌዴሪ የሠላም ሚኒስቴር፤ “ሠላምን በማጽናት በልማት ማንሰራራት” በሚል መርህ ቃል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሠላምና ፀጥታ መዋቅር የባለድርሻ አካላት ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየሰጠ ይገኛል። በመድረኩ ክልላዊ የሠላም ሁኔታ አዝማሚያ ሰነድ በክልሉ የሠላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ምክትል የቢሮ ሀላፊና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ ቀርበው ሰፊ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። የመድረኩ ተሳታፊዎቹ በክልሉ የፀጥታ ስጋት…
ኢሬቻ:-ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት የሚፀናበት ታላቅ እሴት ነው – አቶ ፍቅሬ አማን
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የኢሬቻ በዓል ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነትና ይቅር ባይነት የሚፀናበት ታላቅ ባህላዊ እሴት መሆኑን ገለጹ። አቶ ፍቅሬ ይህንን የገለጹት ለመላው የኦሮሞ ህዝብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች የእንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት ነው። በዓሉ የኦሮሞ ህዝብ የክረምቱን የጨለማ ወቅት አልፎ ወደ ብርሃን ዘመን በሰላም…
የገቢ አሰባሰብ ስረዓት በማሻሻል የክልሉን ገቢ ማሳደግ ተችሏል፦ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ፣በፍቃደኝነት ግብር የመክፈል ባህል እንዲዳብር ለማስቻል ያለመ የባለድርሻ አካላት ምክክር በሚዛን አማን ከተማ አካሂዷል። የክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ፥ የገቢ አሰባሰብ ስርዓት በማሻሻል የገቢ አቅምን ትርጉም ባለው መልኩ ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል። በክልሉ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚውኒኬሽን ተቋማት፣ የሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም…
የሰቆጣ ቃል ክዳን ማስፋፊያ ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ከክልሉ የምግብና ስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ሲያካሄድ የነበረው የሰቆጣ ቃል ክዳን ፕሮግራም የ2017 ዓ.ም የአፈፃፀም ግምገማና የ2018 የጀት ዓ.ም የዕቅድ ዝግጅት መድረክ ተጠናቋል፡፡ በመድረኩ በፕሮግራሙ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆኑ ከሪፓርቱ ለመመልከት የተቻለ ሲሆን በስርዓት-ምግብ ችግር የህፃናት መቀንጨርና የመቀጨጭ ለመቀነስ ፕሮግራሙ በታቀፉ ወረዳዎች ትኩረት ተሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው…
የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና የህዝብ ግኑኝነት አመራሮች የገቢ አሰባሰቡ ውጤታማ እንዲኾን የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ፣በፍቃደኝነት ግብር የመክፈል ባህል እንዲዳብር ለማስቻል ያለመ የባለድርሻ አካላት ምክክር በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። የውስጥ ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የክልሉ ህዝቦች ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የአስተምህሮ ስራ ወሳኝ መኾኑን ነው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በመክፈቻ ንግግራቸው የገለጹት። የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና የሚዲያ አመራሮች በክልሉ የገቢ አሰባሰብ ሥራው ውጤታማ…
