በክልሉ ለኦዲት ግኝቶች ምላሽ በማይሰጡ ተቋማት ላይ የተጠያቂነትና ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፦ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኦዲት ግኝት አስመላሽ ግብረ-ሀይል በኦዲት ግኝት እርምት አወሳሰድ ላይ የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡ በመድረኩ በክልሉ በቤንች ሸኮና በካፋ ዞን በንግድና ኢንቨስትመንት እና በስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ የተደረገውን የክዋኔ እና አካባቢ ኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡ የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ አስራት አበበ ባቀረቡት የሥራ ዕድል…
