“የማሽቃሬ ባሮ”በዓል እሴቶች ለዘላቂ ሰላምና ብልጽግና መሰረት መሆናቸውን ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ
የሸካቾ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሆነው “ማሽቃሬ ባሮ” በዓል የይቅርታ፣ የእርቅና የአንድነት እሴቶቹ ለክልሉ ሰላምና ዘላቂ ብልጽግና ወሳኝ መሰረት መሆናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለመላው የሸካቾ ብሔረሰብና ወዳጆች ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ ማሽቃሬ ባሮ አዲስ ዓመትን ከመቀበል የዘለለ ጥልቅ ማህበራዊና ባህላዊ ትርጉም ያለው…
