የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ በዕድልና በትግል የተሞላ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)::
የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ በዕድልና በትግል የተሞላ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን መርቀዋል፡፡በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግርም ይህንን አስደማሚ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሌሎች የጥቁር ሕዝቦች ሀገራት ሊሠሩት ቢችሉም÷ የምኒልክ ልጅ፣ የባልቻ ልጅ፣ የገበየሁ ልጅ፣ የአሉላ አባ ነጋ ልጅ መሆን ግን አይችሉም ብለዋል፡፡ዕድል ከሌለ ትግል ብቻውን ስኬት እንደማያመጣ…
