ሕብረቱ የመፈጸም አቅሙንና ውጤታማነቱን ለማሳደግ የሰው ኃይል ብቃትና ተወዳዳሪነት ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል፦ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
የአፍሪካ ሕብረት የመፈጸም አቅሙንና ውጤታማነቱን ለማሳደግ የሰው ኃይል ብቃትና ተወዳዳሪነት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ። 23ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በበይነ መረብ ተካሂዷል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በስብሰባው ተሳትፏል። ስብሰባው የተደረገው እ.አ.አ በጁላይ 2024 በጋና አክራ በተካሄደው 45ኛው…
