የሸካቾ ብሄረሰብ የባህላዊ አስተዳደር መዋቅር መሪ በዓለ ስመት ተካሄደ።
የሸካቾ ብሄረሰብ የባህላዊ አስተዳደር መዋቅር ንግሥና ስነስርዓት በሸካ ዞን የነገሥታት መናገሻ በሆነችሁ ጥንታዊቱ የአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ተካሂዷል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካሉት ስድስት የአስተዳደር መዋቅሮች አንዱ የሆነው የሸካ ዞን የድንቅ ተፈጥሮ፤ የብዙ ታሪክና ባህላዊ ዕሴት ባለቤት የኾነ ዞን ነው። “ባህላችን ለአብሮነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በተካሄደዉ የሸካቾ ብሄረሰብ የባህል ሲምፖዚየም የተለያዩ ኩነኔቶች…
