ወጣቶች ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆኑ ሀገር በመገንባት ለትውልድ አሻጋሪ ትልቅ አቅሞች ናቸው ፦ አቶ ነጋ አበራ

“ከቃል እስከ ባህል ” በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የብልጽግና ወጣቶች ክንፍ ሚና በሚል መሪ ሀሳብ ከወጣቶች ጋር የውይይት መድረክ በሚዛን አማን ከተማ ተጀምሯል። በዚሁ ክልላዊ የወጣቶች ክንፍ የንቅናቄ መድረክ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ የብልጽግና ፓርቲ ከዕድሜው…

Read More

ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የሠላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችሉ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ

በክልሉ ብዙኅ ዋና ማዕከላት ከሚገነቡ የክልል ተቋማት ሕንጻዎች አንዱ የሆነው በታርጫ ከተማ የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል። የመሠረተ ድንጋዩን ያስቀመጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በበኩላቸው ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ እየተከናወኑ የሚገኙ የሠላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ላይ ይገኛሉ ብለዋል። ከዚህ ቀደም የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እያስነሱ የሚገኙትን ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶትን በማጠናቀቅና በማስመረቅ እንዲሁም አዳዲሶችንም…

Read More

በከተማው ዘላቂ የንጹህ ውሃ ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በምዕራብ ኦሞ ዞን በማጅ ቱም ከተማ አስተዳደር በባስኬት ፈንዴ ፕሮግራም፤ በውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር በውሃ ልማት ፈንዴ በኩል በተገኘ 55 ከመቶ ብድር እና 45 በመቶ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የወጪ መጋራት ድርሻ የተገነባው የቱም የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አግልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ያነጋገርናቸው የቱም ከተማ ነዋሪዎች፥በከተማው ዘላቂ የንጹህ ውሃ ማግኘት በመቻላቸው መደሰታቸውን…

Read More

“ውጤታማ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለገዢ ትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ በወልቂጤ ከተማ ስልጠናዉ እየተካሔደ ነው፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል እና የፓርቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር ) እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሚዲያና ኮሙኒኬሽን አመራሮችን የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ተገኝተዋል። ውጤታማ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋት የመረጃ ተደራሽነት ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር የሚያስችል…

Read More

“ከቃል እስከ ባህል ” በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ የብልጽግና ወጣቶች ክንፍ ሚና በሚል መሪ ሀሳብ ከወጣቶች ጋር ውይይት በሚዛን አማን ከተማ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ይጀመራል።

በዚሁ ክልላዊ የወጣቶች ክንፍ የውይይት መድረክ ከ700 በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ከወጣው የድርጊት መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል። የወጣቶች ክንፍ የውይይት መድረክ በተዋረድ እስከ ቀበሌ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል። ከውይይቱ ባሻገርም ወጣቶች የደም ልገሳ ፕሮግራም እንደሚያደርጉም ታውቋል። ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተውጣጡ የወጣቶች ክንፍ ትናንት በከተማው እየተከናወኑ ባሉ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በታጠቅ አበበ

Read More

ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የንጹህ መጠጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው የማጅ ቱም የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በምዕራብ ኦሞ ዞን፣ በማጂ ቱም ከተማ አስተዳደር የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከ10ሺህ ለሚበልጡ የአከባቢው ነዋሪዎች አግልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ በባስኬት ፈንድ ፕሮግራም፤ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃ ልማት ፈንድ በኩል በተገኘ 55 ከመቶ ብድር እና 45 በመቶ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የወጪ መጋራት ድርሻ የተገነባ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው 98…

Read More

በጤናው ዘርፍ ሀሩራማ አካባቢዎች የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል ትኩረት በመስጠት ሊሰራ ይገባል ተባለ

የተቀናጀ እና የተሻሻለ የኦንኮ ሰርኪያሲስ በሽታን ማስወገጃ እና ብሔራዊ የጊኒ ዎርም ማጥፋት ፕሮጀክት የማስተዋወቅ መድረክ በሚዛን አማን ተካሂዷል። በፕርግራሙ ማስተዋወቅ መድረክ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ በክልሉ በ5 የተለያዩ በሽታዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱን ተናግረዋል ። የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፋር ክልል የሚገኙ የግብርና እና የኢንደስትሪ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አፋር ክልል በመገኘት የክልሉን የግብርና እና የኢንደስትሪ አቅሞች የሚያሳዩ ቁልፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸው ከስድስት ወራት በፊት ምርት የጀመረውንና 15 ቶን በሰዓት የሚያመርተውን የአዮዳይዝድ ጨው ማምረቻ ምልከታን ያካተተ መሆኑም ተገልጿል። በተጨማሪም በአፋር ክልል የተሳካ የበጋ ስንዴ ምርት እየተካሄደበት ያለውን ልማት ሥራ እና የአይሮላፍ መኖ ባንክ…

Read More

ፍትሃዊ የልማት ስርጭትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ ነው። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

በክልሉ ፍትሃዊ የልማት ስርጭትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በተሰጠው ትኩረት ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት በክልሉ ምዕራብ ኦሞ ዞን ቱም ከተማ የተገነባውን የንጹህ መጠጥ ውሃ መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው። የክልሉ መንግሥት የህዝቡን መሠረታዊ የልማት ጥያቄዎች ለመፍታት ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ትኩረት አድርገው እየሰራ…

Read More

የበሽታ ቅኝትና አሰሳ ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር የህብረተሰቡን ጤና መታደግ እንደሚገባ ተገለፀ

በካርተር ሴክተር በጀት የሚደገፉ የኦንኮ ሰርኪያሲስ፣ በዝሆኔና የጊኒ ዎርም መከታተልና ቁጥጥር የ5ዓመት ፕሮጀክት ዕቀድ ላይ ባለድርሻ አካላት መክረዋል ። የኦንኮ ሰርኪያሲስ፣ በዝሆኔና የጊኒ ዎርም መከታተልና ቁጥጥር ስራዎች በክልሉ ባለፉት 5 ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን የቃኘ የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በፈረንጆቹ ከ2025_2029 ተግባራዊ በሚደረገው ዕቅድ ላይም ተሳታፊዎች ውይይት አድርገዋል። ተሳታፊዎች በቀረቡት የመወያያ ሰነዶች…

Read More