ጫካ ከገቡ የታጣቂ ቡድኖች ጋር ችግሩን በሰላማዊ መንገድ በአጭር ጊዜ ለመፍታት መንግስት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል ፡፡ በዚህም ተጨባች ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡ ሆኖም ከችግሩ ውስብስብነት አንጻር አሁንም በአማራና ኦሮሚያ ክልል ከችግሩ ያለተላቀቁ አካባዎች አሉ፡፡ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመፍታት ምን እየተሰሩ ነው ፤
እንደሀገር የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነትን ከመከላከል አኳያ መንግስት እየሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው፤ የመንግስት የስድስት ወር አፈጻጸም ላይ ባለፈው 2016 ዓ.ም የዋጋ ግሽበት 23 ነጥብ 7 በመቶ የነበረ ሲሆን፤ በ2017 ዓ.ም በታህሳስ ወር ወደ 17 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ የምግብ ዋጋ ግሽበት በ2016 ዓ.ም በታህሳስ ወር 18 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ብሎ ተመዝግቧል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆነው…
