ሁለተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ ሰልጣኝ አመራሮች የቦንጋ ከተማ የከተማ ኮሪደር ልማት እየጎበኙ ነዉ
”በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል ሃሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ2ኛ ዙር በሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ ሰልጣኝ አመራሮች በቦንጋ ከተማ እየተሰራ ያለውን የከተማ ኮረደር ልማት ሥራ እየጎበኙ ይገኛሉ። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት የተጀመረዉ የከተሞች ኮሪደር ልማት ከተሞችን በማስዋብ ገጽታቸውን እየቀየረ ይገኛል። የቦንጋ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ተክለዓብ ቡሎ(ዶ/ር) ለጎብኚዎች…
