በተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 03/2017 ላይ እና በዳኞች ሥነ- ምግባር ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳውሮ ዞን ከፍተኛ፣ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ለተወጣጡ ዳኞች በተሻሻለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በታርጫ ከተማ እየሰጠ ይገኛል። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዳውሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት አቶ አሮታ አልባዞ እንደገለፁት የስልጠናው ዓላማ የዳኝነት አካሉን ግልፅነት እና ተጠያቂነት ባረጋገጠ መልኩ ውጤታማ እና…
