የኢትዮ-ኮደርስ ስልጠና በዲጂታሉ አለም ክህሎት ያለው ዜጋ ለመፍጠር ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተጠቆመ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ለዳውሮ ዞን ታርጫ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በኢትዮ-ኮደርስ ስልጠናና ዲጂታል መታወቂያ ዙሪያ ግንዛቤ አስጨብጧል። የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትልና የስራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አባተ ኡቃ ከ6ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ ተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመው፤በተለይ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሄራዊ…
