ቆይታ ከእኛ ጋር
የትራንስፖርት አገልግሎት ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች እንዲሳለጡ ከፍተኛ ሚና ከሚጫወቱ ዘርፎች አንዱና ዋነኛው መሆኑን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ማረጋገጥ እንችላለን። የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ በአስፈላጊነቱ ልክ በተዋንያኖቹ ምክንያት በሚፈጠሩ ህገ ወጥ አሰራሮች በዜጎች ላይ የኑሮ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችም ሰፊውን ድርሻ እንደሚወስድ አጠያያቂ አይደለም።ከቅርብ ጊዜ ወድህ በዓለም አቀፍ ገበያ ጫና የነዳጅ እና መለዋወጫ እቃዎች ዋጋ…
