ህብረተሰቡ ራሱን ከወቅታዊ በሽታ ለመከላከል ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።
ኅብረተሰቡ ከወቅታዊ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ (Hemorrhagic Fever) ራሱን እንዲከላከል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ አሳስቧል። የቢሮው ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በመልዕክታቸው፥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሽታ ለመጀመሪያ ጊዜ ከታየበት ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አከባቢ ጋር የሚዋሰን በመሆኑ ልዩ ጥንቃቄ ያሻል ብለዋል። በተለይም በክልሉ የምዕራብ ኦሞ ዞን እና የካፋ…
