የእንሰሳት ሀብት ምርታማነትን ለማላቅ የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ስርዓት ተዘርግቶ ወደ ተግባር መግባቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከዞንና ወረዳ ለተውጣጡ የእንስሳት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት የእንስሳት ጤና ፓኬጅ ስልጠና እና ክልላዊ የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። የመድረኩ ዋና ዓላማ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለው ነባራዊ ሁኔታ የሚሰጠውን የእንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽ ከማድረግ አንፃር እና አሁን ባለው ሀገራዊና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታ መነሻ የእንስሳት ጤና…
