ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይል የመገንባት ውጥን ይዛ እየሰራች ነው – ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ
ኢትዮጵያ በ2022 ዓ.ም ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይል የመገንባት ውጥን ይዛ እየሰራች ነው አሉ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ። የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለአካዳሚው ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ተመራቂዎች ለላቀ ግዳጅና አፈፃፀም ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባችኋል፡፡ ኢትዮጵያ የያዘችውን ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይል የመገንባት ውጥን የሚመጥን ቴክኖሎጂና የሰው ኃይል…
