ነዋሪዎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ሁለተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሥራት ከባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ተባለ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የከተማ ሴፍትኔት ሥራ ፕሮጀክት(UNSNJP) እና የመንግስት ተዛማጅ ፈንድ(GME) የ2016/17 አፈጻጸም ሪፖርትና የ2017/18 ጠቋሚ ዕቅድ ላይ የክልሉ ስተሪንግ ኮሚቴ በሚዛን አማን ከተማ ውይይት አካሂዷል። የሴፍትኔት ፕሮግራሙ አቅመ ደካሞችን በከተማ ግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በከተማ ቆሻሻ ማፅዳት፣ በአረንጓዴ ልማትና በሌሎች የአካባቢ ልማት ስራዎች ከግንዛቤ እስከ ምርት ድረስ እየደገፈ መሆኑ ተጠቅሷል። መድረኩን የመሩት የክልሉ ከተማ…
