የአርብቶ አደሩን ሕይወት በዘላቂነት በመቀየር የተረጋጋ ኑሮ እንዲመራ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ገለጸ።
በቢሮው ከፍተኛ አመራሮች የተመራ ልዑክ በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የሚሠሩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል። በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ የሚሠሩ የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ የልማት እና የፕሮጀክት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና በዘላቂነት የተረጋጋ ኑሮ እንዲመሩ በክልሉ መንግሥት በኩል ሰፊ ስራ እየተሠራ መሆኑን የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ኋላፊ አቶ መቱ አኮ ተናግረዋል። ሱሪ ወረዳ ለተለያዩ የሰብል…
